1. የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ በሰው፣ በእነስሳትና በአካባቢ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት
እያደረሰ ያለ አለምአቀፍ ችግር ነው፡፡
2. የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በሰውና እንስሳት ላይ የሚደርሱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከልና ለማከም
የምንጠቀማቸው ሲሆኑ እነዚህን መድኃኒቶች ያለ ሀኪም ትዕዛዝ አይውሰዱ! ለሌላም ሰው አያጋሩ!
3. በፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ምክንያት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች ለከፍተኛ
የጤና፣የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ!
4. መድኃኒት ለማያስፈልጋቸው ወይም ሰውነታችን በተፈጥሮ ባለው ሃይል ሊቋቋማቸው ለሚችሉ ህመሞች
የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶችን አይውሰዱ፤
5. ጥቅም ላይ ያልዋሉ ወይም የመጠቀሚያ ግዜያቸው ያለፈ የፀረ-ተህወስያን መድኃኒቶችን ያለአግባብ በቆሻሻ
መልክ አይጣሉ!