ግብርናን በማዘመን ሂደት ውስጥ የምርምር ተቋማት ሚና ወሳኝ እንደሆነ ተጠቆመ

Mar 28 2020

በግብርና ሚኒስቴር የብሄራዊ እንስሳት ጤና ምርምራ እና ጥናት ማዕከል 25 ዓመት የብር ኢዩቢሊዩ በዓል ከህዝብ ተወካዮች /ቤት የግብርና አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የግብርና ሚኒስቴርና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የእንስሳት ምርምር ተቋማት ሃላፊዎች እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የካቲት 07/2012 . በሰበታ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

25 ዓመት የብር ኢዩቢሊዩ በዓሉን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ዑመር ሁሴን እንደገለፁት ማዕከሉ በአገራችን የእንስሳት ልማትን ለማሳደግ፣ የእንስሳት ጤና ጥበቃና ምርታማነት በማሻሻል አንዱና ዋናኛ ተዋናይ በመሆን ላደረገው አስተዋፆ ምስጋናቸውን አበርክተዋል። አክለውም በሀገር አቀፍ ደረጃም በተለያዩ ወቅቶች በሽታዎች ሲከሰቱ የአሰሳና ቅኝት ስራዎችን በመስራትና መንስኤዎቹ በመለየት የቁጥጥርና የመከላከል ስራዎችን ጨምሮ ሲያካሂድ መቆየቱን ገልፀዋል።

/ ተስፋዬ ሩፋኤል የብሄራዊ እንስሳት ጤና ምርምራ እና ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር በበኩላቸው ማዕከሉ 1987 . ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስኬታማ ስራዎችን አከናውናል ይህንን በማስመልከትብሄራዊ እንስሳት ጤና ምርምራና ጥናት ማዕክል ወደ ፊት በመገስገስ ላይበሚል መሪ ቃል እያከበረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ማዕከሉ ካከናወናቸው በረካታ ስኬታማ ስራዎች ውስጥ የተወሰኑትን እንዲህ ይጠቅሳሉ፤ አስራ አራት አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ምርመራዎችን በሲሮሎጂና በሞሎኩላር የምርመራ ዘዴ ማካሄድ መቻሉ፣ የበሽታ ምርመራና ምርምር ማካሄድ መቻሉ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደስታ በሽታ ማጥፋቱ፣ የተላላፊ የፍየል ሳምባ ነቀርሳና አባሰንጋ በሽታ መቆጣጠር ድንበር ዘለል ለሆኑ የእንስሳት በሽታዎች ለምስራቅ አፍሪካ ድጋፍ ስጪ ላቦራቶሪ ሆኖ መመረጡ ባለፉት 25 የስኬት አመታት ካከናወናቸው ተግባራት በጥቂቱ መሆኑና ይህንን ልምድ በማዳበር በቀጣይ አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን ለመተግበር ስንቅ የሰነቀ እንደሆነ ይገልፃሉ።

ማዕከሉ 35 በላይ የምርምር ፅሁፎችን በመስራት ለፖሊሲና ስትራቴጂ ነደፋ ግብዓትነት ማዋል ከማስቻሉ ጎን ለጎን ከግብርና ሚኒስቴር ባገኘው ድጋፍ የማይክሮ ባዮሎጂ ላቦራቶሪ እንዲሁም ማዕከሉ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን የሚያካሂድበት ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽ በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ መገንባቱ ከማዕሉ የተገኝው መረጃ ያስረዳል። የስብሰባ አዳራሹም የማእከሉ ዳይሬክተር ሆነው ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ በነበሩትና በቅርቡ በሞት በተለዮት በዶ/ር መስፍን ሳህሌ ስም ተሰይሟል፡፡ 

በዓሉም የተለያዩ ደማቅ ዝግቶች ተካሂደውበታል፡፡ ለአብነትም በማዕከሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላገለገሉና አሁንም በማገልገል ለሚገኙ ባለሙያዎች ከሚኒስትሩ የዋንጫና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፣በማዕከሉ የተገነባ የስብሰባ አዳራሽ ምርቃት፣ ማዕከሉ በዘመናዊ ላቦራቶሪዎች ስራዎችን እንዴትያከናወነ እንደሚገኝ በአመራሩ ጉብኝት ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም የተከበሩ አቶ ዑመር ሁሴን - የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ሀብት ልማትን ለማዘመን እና ሀገራችን ከዘርፉ ማገኝት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል በመኖ ልማት የእንስሳት ጤና አጠባበቅና የግብይት ስርዓት ዘርፉን የሚደግፉ ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች ቅንጅት በመፍጠርና የመፈፀም አቅማቸውን በማሳደግ ለተሻለ ውጤት ተግተው መስራት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

 

NAHDIC - 25 Years